ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብር ሊያካሂድ ነው

You are currently viewing ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብር ሊያካሂድ ነው

AMN – ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብር ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራዳ ፓርክ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ የሰላምና የጸሎት መርሃ ግብርን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመግለጫቸው፣ ሀገር አቀፍ የሰላምና የአብሮነት የጸሎት መርሃ ግብሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚሳተፉበት ነው።

በመርሐ ግብሩ የሰላም እና የአብሮነት መልዕክቶችን ማስተላለፍ፣ የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ፣እንዲሁም በህዝቦች መካከል ሰላምና አብሮነትን ማጠናከርና ለሀገር መቆም ዋነኛ ትኩረቱ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ በማግኘት በመርሐ ግብሩ ላይ እንዲሳተፍ የመገናኛ ብዙኃን ኋላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ግንቦት 16 ቀን 2018 ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው መርሐ ግበር የጋራ እሴቶችና አንድነትን የሚያጎሉ መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ጠቅሰዋል፡፡

ለሀገር ዘላቂ ሰላም፣ለሕዝቦች መተሳሰብ እና አብሮነት መጽናት በጋራ ጸሎት እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

ጉባኤው ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ወቅቶች መሰል ሀገር አቀፍ የጸሎት መርሐ ግብሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የሁሉም የጉባኤው አባል ቤተ-እምነት ተቋማት የሃይማኖት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አስታውሰዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review