የኤ ኤም ኤን የ“አሸናፊ ትውልድ” የሩጫ ውድድርን በወንዶች አዲሱ ጌትነት እና በሴቶች ተዓቢ ጌትነት አሸናፊ ሆኑ

You are currently viewing የኤ ኤም ኤን የ“አሸናፊ ትውልድ” የሩጫ ውድድርን በወንዶች አዲሱ ጌትነት እና በሴቶች ተዓቢ ጌትነት አሸናፊ ሆኑ

AMN- ሰኔ 28/2018 ዓ.ም

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ“አሸናፊ ትውልድ” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን በወንዶች አትሌት አዲሱ ጌትነት እና በሴቶች አትሌት ተዓቢ ጌትነት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ“አሸናፊ ትውልድ” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

መነሻውን ዓድዋ ድል መታሰቢያ እና መዳረሻውን ቀበና ባደረገው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በወንዶች አትሌት አዲሱ ጌትነት 1ኛ ደረጃ፣ አትሌት ሰውመሆን አንተነህ 2ኛ ደረጃ፣ አትሌት ሃለፎም ተስፋዬ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡

እንዲሁም በሴቶች ተዓቢ ጌትነት ከፀደይ ባንክ 1ኛ ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ጥበብ እንየው ከአማራ ማረሚያ 2ኛ በመሆን እንዲሁም ማርታ ቦርማ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

በመርኃ ግብሩ የኤ ኤም ኤን የ“አሸናፊ ትውልድ” የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር አሸናፊዎች የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review