የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 118 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

AMN – ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም

የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን እና የደንበኞችን ቁጥር በማስፋት በ2018 በጀት አመት ብቻ 118.9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ተቋሙ የ2018 በጀት አመት አፈፃፀም እና የ2019 በጀት አመት እቅድን እየገመገመ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ የኤሌትሪክ አገልግሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፤ ተቋሙ ባለፈው በጀት አመት የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን እና የደንበኞችን ቁጥር በማስፍት በ2018 በጀት አመት ብቻ 118.9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘት ችሏል፡፡

አገልግሎቱን ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ባለፈው በጀት አመት ብቻ 664 ሺ 505 አዳዲስ ደንበኞችን ማገናኘት ስለመቻሉ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፤ ይህም በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በአለምም ከቻይና እና ህንድ ቀጥሎ ቀዳሚ ያደርገናል ብለዋል፡፡

በተለይ በገጠር ከተሞችን የኤሌትሪክ ሀይል ተደራሽነትን ማስፍት የበጀት አመቱ ስኬት ስለመሆኑ ያነሱት ኢንጅነር ጌቱ ገረመው፤ በዚህም 205 የገጠር ከተሞችን ማገናኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

እነዚህን ስራዎች በመስራት ሂደት ውስጥ አሁንም እንቅፋት ሆነው የዘለቁት በተቋሙ ንብረት ላይ የሚደርሱ የስርቆት ወነጀሎች መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

በበጀት አመት ብቻ 570 ሚሊየን የሚገመት ንብረት መዘረፉን አስታውሰው፤ ስርቆትን በመከለከል 2.2 ቢሊየን ብር ደግሞ ማትረፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review