“ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የአፍሪካ በራሷ እጣ ፈንታዋን የመወሰን ጉዞ ማሳያ ነው”-ኡሁሩ ኬንያታ

You are currently viewing “ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የአፍሪካ በራሷ እጣ ፈንታዋን የመወሰን ጉዞ ማሳያ ነው”-ኡሁሩ ኬንያታ

AMN- ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም

በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ጉባኤው አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው የመፍታትና እጣ ፈንታቸውን የመወሰን አቅማቸውን ያሳየ አህጉራዊ ኩራት መሆኑን ገለጹ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው ይህ ጉባኤ የቆዩ የታሪክ ቁርሾዎችን ለመፍታት ትልቅ መንገድ የከፈተ መሆኑን የጠቆሙት ኡሁሩ ኬንያታ፤ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ አካላት መሳተፋቸው ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አካታች፣ ብዝሃ ድምጾች የተሰሙበትና የሀገር ፍቅር ስሜት የተንጸባረቀበት እንደነበር አብራርተዋል።

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ህያው መዲና መሆኗን ያሰመሩበት የቀድሞው ፕሬዝዳንት፤ አህጉሪቱ ለገጠሟት ፈተናዎች ዘላቂ መፍትሔዎችን ስትፈልግ ሁልጊዜም ዞር ብላ የምታየው ወደዚች ታሪካዊ የአፍሪካ መዲና መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታሪክ የጽናት እና የአይበገሬነት ምልክት መሆኑን ያብራሩት ኬንያታ፤ የአድዋ ድል ለአፍሪካ የነጻነት ትግልና ከቅኝ ግዛት ነጻ መውጣት ትልቅ መሰረት የጣለ መሆኑን አብራርተዋል።

በመጨረሻም ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ መስራች፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የጥንታዊ አፍሪካውያን ስልጣኔ መገለጫ መሆኗን በማስታወስ፣ በጉባኤው ላይ ለተሳተፉ እና ለሂደቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review