5ቱ የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ ማንሠራራት በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራሉ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN- ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

የ2018 ዓ.ም 5ቱ የጳጉሜን ቀናት የኢትዮጵያ ማንሠራራት በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ገለጹ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ፤ የጳጉሜን ቀናት አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም፤ 5ቱ የጳጉሜን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች በመላው ኢትዮጵያ እንደሚከበሩ በመግለጽ ቀናቱ የኢትዮጵያ ማንሠራራት በሚል መሪ ቃል ይከበራሉ ብለዋል፡፡

ጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን፣ ጳጉሜን 2 የማንሠራራት ቀን፣ ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን፣ ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን፣ ጳጉሜን 5 የነገ ቀን በሚል ስያሜ በተለያዩ ሁነቶች ተከብረው ይውላሉም ነው ያሉተ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ የጳጉሜን ቀናትን በተለያዩ ስያሜዎች እና የአከባበር ሥነ-ስርዓት እንዲሁም መሪ ሃሳብ ሲከበር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ጳጉሜን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ልዩ ወር እና መለያ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የዓመቱ መሸጋገሪያ ወር በመሆኑ የዓመቱን ሃገራዊ ስኬቶች የምንገመግምበት እና ክፍተቶችን የምናስተካክልበት እንዲሁም ለቀጣይ አቅጣጫ የሚተለምበት ወር በመሆኑ ቀናቱን ማክበር አስፈልጓል ብለዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review