
AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ ያቀረበውን የስንብት ውሳኔ አስመልክቶ የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ተገልጿል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።