የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስብራቶች ማብቂያ የተበሰረባት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን የመጡባት፣ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የተያዘባት መጋቢት 24 በከተማ ደረጃ በፓናል ውይይት መከበር ጀምሯል።
ሀገራዊ ለውጥ የጀመረበትን 7ኛ ዓመት “ትናንት፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስብራቶች ማብቂያ የተበሰረባት ፣ ኢትዮጵያን የሚያሻግር አዲሱ የመደመር አሳቤ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስቻለው ሀገራዊ ለውጥ ዕውን የሆነባት፤ ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋጥ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማብሰር መሰረት የተጣለባት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመቆም ተቃርቦበት ከነበረበት የታደገው ሀገራዊ ለውጥ ዕውን የሆነባት፤ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት ወደከፍታዋ የሚወስዳትን መንገድ የቀየሱት የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸናፊው ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡባት፤ አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የተያዘባት መጋቢት 24 በከተማ ደረጃ በፓናል ውይይት መከበር ጀምሯል።
በፓናል ውይይቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።