የኢትዮጵያውያንን አስተዋይና የጀግንነት ባህሪ በአርቆ አሳቢነት መንገድ አፅንቶ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ተናገሩ

You are currently viewing የኢትዮጵያውያንን አስተዋይና የጀግንነት ባህሪ በአርቆ አሳቢነት መንገድ አፅንቶ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ተናገሩ

AMN ጥር 11 /2018

የኢትዮጵያውያንን እውነትን ወዳድነት፣ ትዕግስት፣ አስተዋይና የጀግንነት ባህሪ በአርቆ አሳቢነት መንገድ አፅንቶ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።

በታሪካዊቷ ጎንደር የፋሲለደስ ጥምቀተ ባሕር የጥምቀት በዓል ኃይማኖታዊ ትውፊትና ሥርዓቱን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በአከባበር ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጎንደርን ከሚያደምቁ ዐበይት መንፈሳዊና ኃይማኖታዊ በዓላት መካከል ጥምቀት ግንባር ቀደሙ ነው ብለዋል።

የጎንደር የኪነ-ሕንፃ የጥበብ አሻራም የሚታይና የሚዳሰስ ታሪካዊ ፀጋ መሆኑን ገልጸዋል።

የጎንደር ህዝብ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለሰው ልጅ የላቀ ክብርና ፍቅር ያለው እንደሆነም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያዊነት መገለጫው ስክነትና አስተውሎት ነው ያሉት ፕሬዝዳንታ ታዬ፥ ይህን የብልህ መንገድም መከተል ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያውያንን እውነትን ወዳድነት፣ ትዕግስት፣ አስተዋይና የጀግንነት ባህሪ በአርቆ አሳቢነት መንገድ አፅንቶ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሰልፏ በፍጥነት ከሚገሰግሱና ከሚራመዱት ጋር መሆን እንደሚኖርበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተለዋዋጭ የዓለም አቀፍ ሁኔታም ኢትዮጵያውያን አርቆ ማስተዋልና በተረጋጋ ሁኔታ መመልከት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

በአንድ ዓመት ውስጥ ያየሁት ለውጥ አስደናቂ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ ሀሳብ ትውልድና አመራር ሲስማማ ታሪክ መሥራት እንደሚቻል ጎንደር ማሳያ ናት ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የጎንደር ከተማን ዳግም ውልደት በተግባራቸው ለወጁ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ትጉህ ልጆች ካሉ ግን ተስፈንጥሮ መሄድ እንደሚቻል በጎንደር ታይቷል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ ሀሳባችን ታፍራና ተከብራ የምትኖረውን ኢትዮጵያ ማፅናት ነው ማለታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review