ትዕግስት አሰፋ የዓለም ፈጣን ሯጭ በሚል በዓለም ድንቃድንቅ ተመዘገበች

You are currently viewing ትዕግስት አሰፋ የዓለም ፈጣን ሯጭ በሚል በዓለም ድንቃድንቅ ተመዘገበች

AMN ሚያዝያ 19/ 2018 ዓ.ም

ትዕግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ በተደረገው የለንደን ማራቶን ውድድር ላይ 2:15:41 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የሴቶች የዓለም ክብረ ወሰንን አሻሽላለች።

ትዕግስት በመጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትሮች ላይ ፈጥና በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የለንደን ማራቶን አሸናፊ ሆናለች። በዚህ ድሏም የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ እውቅና ሰጥቶ በመዝገቡ አስፍሯታል፡፡

በወንዶች ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ 42 ኪሎ ሜትሩን በ1:59:30 በማጠናቀቅ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን በይፋዊ ውድድር ከሁለት ሰዓት በታች የገባ ፈጣኑ ሯጭ ተብሏል፡፡ ስሙም በጊነስ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍሯል።

በዚህ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች በሆነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በርቀቱ የኢትዮጵያ ክብረወሰን ባለቤት ሆኗል።

የዘንድሮው የለንደን ማራቶን በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን 59ሺህ ተሳታፊዎችን ያስተናገደ እና በክብረወሰኖች የታጀበ ድንቅ ውድድር ሆኖ ማለፉን ተዘግቧል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review