ህብረ-ብሔራዊት በሆነችው ከተማችን ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ እየሰራን እንገኛለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ህብረ-ብሔራዊት በሆነችው ከተማችን ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ እየሰራን እንገኛለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

በኅብር ቀን አሮጌውን ዓመት አልፈን ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን ከሚያበስሩ ውብ እና ህብራዊ ባህሎቻችን መካከል የሆኑትን የአበባአየሽ ወይ፣ የአሸንዳ፣ ጎቤ፣ ሽኖዬ፣ ሻደይ ጭፈራዎች በከተማችን በታሪካዊው የአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብረዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ የበለፀገ የህብረተሰብ ሀብት ክምችት ያላት ሀገር ናት። የመደመር መንግሥትም እነዚህን ሀብቶች በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማልማት ለሀገር እድገትና ለህብረተሰብ ልማት ማዋል ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ህብረ-ብሔራዊት በሆነችው ከተማችንም ውብ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችን ጎልተው እንዲወጡ፣ ከባህሉና እሴቱ ማግኘት የሚገባንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ እና የቱሪዝም መስህብ እንዲሆኑ እየሰራን እንገኛለን ሲሉም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review