በአመቱ በሀገር፣ በአሕጉርና በአለም አቀፍ ደረጃ በላቀ አፈፃፀማቸው እና በተቀናጀ አገልግሎት የክብር ሽልማት ከዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተበርክቶላቸዋል።
በልዩ የተቋም የአመራር ብቃት ልህቀት ከፍተኛ ዲፕሎማ ሽልማት ተሸላሚዎች የሀገር አውታር፣ የኢኮኖሚ ደጋፊ የሥራ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያን ናቸው።
በ20ኛው የግራንድ አፍሪካ የተቋማትና የአመራር ሽልማት መርሐ ግብር የዳይመንድ ዋንጫ ተሸላሚዎች:-
1. ሼክ ቱፊክ ሲራጅ የቲ ኬ ትሬዲንግ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ
2. አቶ ሳሙኤል ታፈሰ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን መሥራችና ሥራ አስኪያጅ
3. አቶ ተፈራ ለማ ጂማ የሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ
4. አቶ ገምሹ በየነ የኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት
5. አቶ በላይነህ ክንዴ መኮንን በላይነህ ክንዴ ኢንቨስትመን ጉሩፕ ባለቤት
6. ዶ/ር አብዱልሀኪም ሙሐመድ ጀላቶ የኤ ኤም ጂ ግሩፕ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ
7. ዶ/ር እስራኤል ደግፌ ስሜ የቀርጫንሼ ትሬዲንግ ፒ ኤል ሲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ናቸው።
በበረከት ጌታቸው